የሀገር ውስጥ ዜና

ሀገር በቀል የኢንዱስትሪዎችን አቅም ማሳደግ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና ምሰሶ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

By Meseret Awoke

May 07, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር በቀል የኢንዱስትሪዎችን አቅም ማሳደግ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና ምሰሶ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።

የ”ኢትዮጵያ ታምርት” መርሃ ግብር ማስጀመሪያ በቤተ መንግስት የተካሄደ ሲሆን ፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ለ81 አምራቾች እውቅና ተሰጥቷል።

በመርሃ ግብሩ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በ2022 ለማሳካት የታቀደውን እቅድ ለማሳካት የማምረቻ ዘርፉን ውጤታማ የማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን አንስተዋል።

የሀገር ውስጥ ምርት መጀመር ከውጭ ምንዛሬ ማዳን እስከ ስራ እድል ፈጠራና የወጭ ንግድ ማሳደግ ሚና እንዳለውም ጠቅሰዋል።

በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ጥናት መጠናቱን በማንሳትም ለመፍትሄዎቹ የክልልና የፌዴራል መንግስታትን ቅንጅት ይጠይቃል ነው ያሉት።

በአስቸጋሪ ጊዜያት ሀገር በቀል አምራቾች ለኢትዮጵያ መቆማቸውን በመጥቀስም አመስግነዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበኩላቸው ፥ በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ባለሀብቶችም ሀገራቸው መሆኗን በመረዳት ለመፍትሄው መጣር አለባቸው ብለዋል።

በግብርናው ዘርፍ ውጤታማነት መመዝገቡን በማንሳትም ይህን ውጤት በኢንዱስትሪው ዘርፍ መድገም ይገባልም ነው ያሉት።

ሀገር በቀል የኢንዱስትሪዎችን አቅም ማሳደግ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና ምሶሶ እንደሆነም ነው የገለጹት።

በአፈወርቅ እያዩና በርናባስ ተስፋዬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡