Fana: At a Speed of Life!

የበጋ የስንዴ ምርት በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የበጋ የስንዴ ምርት በተሳካ ሁኔታ እየተናወነ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ የስንዴ ምርት በተሳካ ሁኔታ እየተከነወነ እንደሆነ ገልጸው “በጋራ በቀደሙት በስኬቶቻችን ላይ አብሮ የከተማ ግብርና ታክሎበት የምግብ ዋስትና ተግዳሮቶችን ቀስ በቀስ መፍታት ያስችለናል” ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተገባደደው በዚህ ወር በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሲያደብርና ዋዩ ወረዳ በመስኖ የለማ ስንዴን መጎብኘታቸው ይታወሳል ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት በአማራ ክልል የስንዴ ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገውን ከፍተኛ ጥረት አደንቃለሁ ብለዋል።

“በክላስተር የግብርና አካሄዳችን በአንድነት ለምግብ ዋስትና እና ለሀገር ልማት ምን እንደምናሳካ ማሳያ ነው” ማለታቸውም ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.