Fana: At a Speed of Life!

የዳሽን ቢራ ፋብሪካ በ1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ያካሄደውን የማስፋፊያ ፕሮጀክት አጠናቆ አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዳሽን ቢራ ፋብሪካ በ1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ወጪ ያካሄደውን ማስፋፊያ ፕሮጀክት አጠናቆ በዛሬው እለት አስመርቋል።
በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ተገኝተዋል፡፡
አቶ ደመቀ በስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ፕሮጀክቱ የሰላምና የልማት ዋጋን ጥምረት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
ይዚህ ፋብሪካ ማስፋፊያ የቴክኖሎጂ አቅምን በማሳደግ ለብልጽግና ተደማሪ አቅም እንደሚሆንም እንጠብቃለን ነው ያሉት ፡፡
በሃገሪቷ ሁሉም አካባቢዎች የልማት ውጥኖች ከግብ እንዲደርሱ የሰላምና ጸጥታ ችግሮችን ለመፍታት በጥልቀት እየተሰራ መሆኑንንም ተናግረዋል።
ለዚህ ደግሞ ማህበረሰቡም የሰላሙ ባለቤት ነውና በሁሉም አከባቢ የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ የሃገሪቷን የልማት እቅድ ለማሳካት ሁላችንም በጋራ ልንሰራ ይገባል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በበኩላቸው፥ የዳሽን ቢራ ፋብሪካ ወደ ደብረ ብርሃን መምጣትን ተከትሎ ለሌሎች ፋብሪካዎች መስፋፋት መንገድ ከመክፈቱም ባለፈ ለአካባቢው አርሶ አደሮችም ምርታቸውን ለገበያ ለማቅረብ ትልቅ እድልን ይዞ የመጣ መሆኑን አንስተዋል።

ከዚህ ባለፈ ፋብሪካው ከዚህ ቀደም ከውጭ ያስገባ የነበረውን የብቅል ግብአቱን አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ በሃገር ውስጥ እንዲተካ በማድረግ የውጭ ምንዛሬ ወጪንም መታደግ ችሏል ተብሏል።
በአማራ ክልል በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አይናለም ንጉሴ÷ የዳሽን ቢራ ፋብሪካ በሰሜን ሸዋ እያደገ ለመጣው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ አንዱ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል፡፡
መንግስት ለስራ እድል ቅድሚያ ለሰጠው ተግባርም የተደረገው ማስፋፊያ የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ያደርገዋልም ነው ያሉት።
በይስማው አደራው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.