Fana: At a Speed of Life!

የሸዋል ኢድ በዓል በሀረር ከተማ መከበር ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢድ እስከ ኢድ ሀገራዊ ጥሪ አካል የሆነውና የሀረሪ ብሔረሰብ መገለጫ የሆነው የሸዋል ኢድ በዓል በሀረር ከተማ በይፋ መከበር ጀምሯል፡ ፡
የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አርዲን በድሪ ÷ የሸዋል ኢድ “የኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት” ጥሪ አንዱ አካል መሆኑን ጠቁመው ጥሪውን ተከትሎ የመጡትም ተሰባስቦ በዓልን ከማክበር ባለፈ ኢትዮጵያ ያሏትን ተፈጥሯዊ፣ ጥንታዊና ሰው – ሠራሽ መስህቦችን በመጎብኘትና በማስተዋወቅ፣ በኢንቨስትመንት በመሣተፍና በሀገራችን እየደረሰ ያለውን የውጭ ጫና ለመመከት በዲፕሎማሲ መስክ የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠይቀዋል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሣ በበኩላቸው ÷ጥንት እናት አባቶቻችን ያቆዩልንና ያወርሱንን ዘመን- ተሻጋሪ ቅርሶችና አኩሪ እሴቶችን በመጠበቅና እሴት በመጨመር ከዘመኑ ጋር እያዘመኑ ለቀጣዩ ትውልድ ከማስተላለፍ አንፃር የወጣቱ ትውልድ ሃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል።
የሸዋል ኢድ በዓለ በሀረሪ ብሔረሰብ አባላት ዘንድ የኢድ አልፈጥር በዓል ከተከበረ በኋላ ለተከታታይ 6 ቀናት ከተፆመ በኋላ ፈላና በርና ኤረር በር በተባሉት ሁለት የጀጎል በሮች በዋናነት ይከበራል፡፡
የበዓሉን አከባበር በተመለከተ በቀረበ ፅሁፍ ከ500 ዓመታት በላይ ሲከበር የቆየ የሀረሪዎች ባህላዊ በዓል መሆኑና የመሰባሰቢያና የመገናኛ እንዲሁም የመተጫጫ መድረክ እና አንድ የቱሪስት መስህብ ስለመሆኑ ተመልክቷል።
በዓሉ በይፋ መከፈቱ በተሰረበት የውይይት መድረክ ላይ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አርዲን በድሪ እና የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ከአምስቱ የምስራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነውበታል።
በተሾመ ኃይሉ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.