በባርሴሎና የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1 እስከ 3 በመውጣት በበላይነት አጠናቀቁ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በባርሴሎና የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1 እስከ 3 በመውጣት በበላይነት አጠናቀቁ ፡፡
በስፔን ባርሴሎና ማራቶን በተካሄደ የወንዶች የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1 እስከ 3 በመውጣት ያለውን ደረጃ በመያዝ በበላይነት ማጠናቀቃቸውን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገነነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ውድድሩን አትሌት ይሁንልኝ አዳነ 2 ሰዓት 5 ደቂቃ 52 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት አሸንፏል፡፡