Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ 6ኛውን የኢትዮጵያ ሕግ ትምህርት ቤቶች ምስለ ችሎት ውድድር አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሚያዚያ 27 እስከ 30 ቀን 2014 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እና በኢፌዴሪ ፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተካሄደው 6ኛው የኢትዮጵያ ሕግ ትምህርት ቤቶች ምስለ ችሎት ውድድር በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ውድድሩ ለሁሉም የኢትዮጵያ የሕግ ትምህርት ቤቶች ክፍት የሆነ ሲሆን÷ በቃል ክርክሩ ላይ የሚሳተፉ ዩኒቨርሲቲዎች በውድድሩ የጽሑፍ ዙር ባስመዘገቡት ውጤት የተመረጡ ናቸው።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ኮሌጅ የውድድሩ አሸናፊ ከመሆኑ በተጨማሪ ለውድድሩ ከተዘጋጁ አምስት ዋንጫዋች አራቱን መውሰዱን የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመላክታል፡፡
በሌላ በኩል የውድድሩ የጽሑፍ ዙር በተደረገው ውድድር ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የውድድሩ ምርጥ ጽሁፍ (ቤስት ሚሞሪያል) አሸናፊ ሆኗል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.