Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ሣምንት እያከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ምርምሮችን የሚያቀርብበትን የ2022 የምርምር ሣምንት “የልህቀት ማእከሎች የለውጥ መሪዎች” በሚል መሪ ቃል ማክበር ጀመረ፡፡
በ10 ዓመቱ የዩኒቨርሲቲው ስትራቴጂክ እቅድ÷ ተቋሙን ከአፍሪካ የምርምር ተቋማት መካከል ለመመደብ አቅዶ ሲሠራ እንደቆየ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና ተናግረዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ምትኬ ሞላ በበኩላቸው÷ ዩኒቨርሲቲው በምርምር ስራ በአለም ላይ የሚታወቅ ተቋም ነው ብለዋል።
በመክፈቻ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ÷ ምርምር ከዓለም አቀፉ ዘላቂ ልማት ግብ ጋር የበለጸገች አፍሪካን ለመፍጠር ከሚያልመው አጀንዳ 2063 ጋር እንዲሁም ለኢትዮጵያ ደግሞ ከታቀዱ የሀገሪቱ የልማት አቅጣጫዎች ጋር ተጣጥሞ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል።
በ10 አመቱ የሀገሪቱ እቅድ በተለይም በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በማዕድን ልማት፣ በቱሪዝም እና በዲጂታል ልማት ዘርፉ ምርምሮች እንደሚያስፈልጉ እና ለዚህም መሰል የምርምር ሣምንት ዝግጅቶች አጋዥ እና አስታዋሽ ናቸው ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲው ባዘጋጀው የምርምር ሣምንት በቀጣይ ቀናት የተለያዩ የምርምር ስራዎች የሚቀርቡና እየቀረቡ ውይይት የሚደረግባቸው መሆኑም ተመላክቷል፡፡
በተስፋዬ ከበደ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.