ጥላቻና ግጭት እንዲፈጠር የሚሰሩ ማህበራዊ ድረ ገጾች ለሀገሪቱ ተግዳሮት ናቸው- የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥላቻና ግጭት እንዲፈጠር የሚሰሩ ማህበራዊ ድረ ገጾች ለሀገሪቱ ተግዳሮት መሆናቸውን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ገለጸ፡፡
ለ31ኛ ጊዜ “ጋዜጠኝነት በዲጂታል ዓለም ውስጥ” በሚል መሪ ቃል የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን እየተከበረ ነው፡፡
በዚህ ወቅት የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ሰብሳቢ አማረ አረጋዊ ÷ በሀገሪቱ ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነት እንዲሰፍን ማህበራዊ ድረ ገፆች የጋዜጠኝነት ስነምግባር መመሪያ መሰረት ተግባራቸውን ማከናወን አለባቸው ብለዋል፡፡
እየተስፋፋ ያለው የማህበራዊ ድረ ገጾች አጠቃቀም÷ በተለይም በኢትዮጵያ ማህበራዊ ኃላፊነት በጎደለው እና የጋዜጠኝነት ስነ ምግባርን ባልጠበቀ መልኩ የሚለቀቁ ግጭት ቀስቃሽ መረጃዎች ለሀገሪቱ ተግዳሮት መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡
በታሪኩ ለገሰ