የሀገር ውስጥ ዜና

በጅግጅጋ ከተማ “ስለ ኢትዮጵያ” የተሰኘ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ ተከፈተ

By ዮሐንስ ደርበው

May 09, 2022

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን ለማዳን በሕግ ማስከበርና በህልውና ዘመቻው ወቅት ያደረጉትን ተጋድሎ የሚያሳይ “ስለ ኢትዮጵያ” የተሰኘ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ በጅግጅጋ ከተማ ተከፈተ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ አቶ ጉባኤ ታገሰ ጫፎና የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ “ስለ ኢትዮጵያ” የተሰኘውን የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ መርቀው ከፍተዋል።

የፎቶግራፍ አውደ ርዕዩ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ለሕዝብ ዕይታ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን÷ በሌሎችም ክልሎችም የሚቀጥል መሆኑ ተገልጿል።

ከፎቶ አውደ ርዕዩ ቀጥሎ “ኢትዮጵያ እያሸነፈች ትሻገራለች” በሚል መሪ ሐሳብ የፓናል ውይይት ይካሄዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል፡፡