Fana: At a Speed of Life!

የቡድን 7 አባል ሀገራት የሩሲያ ነዳጅ ዘይት ላይ እገዳ ሊጥሉ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡድን 7 ሀገራት የሩሲያን ነዳጅ ዘይት ወደሀገራቸው እንዳይገባ እገዳ ሊጥሉ መሆኑ ተሰማ።
ሀገራቱ በሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ ጫና ለመፍጠር በሚል የሩሲያ ነዳጅ ዘይት ጥቅም ላይ እንዳይውል ወይም ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ ሊወስኑ መሆኑን ከኋይት ሃውስ የወጣው መግለጫ ያመላክታል፡፡
ይህም ሩሲያ ከዩክሬን በገባቸው ጦርነት የፕሬዚዳንት ፑቲንን የኢኮኖሚ ምንጭ በመቀነስ ለጦርነቱ የሚያስፈልገውን ገቢ ለማሳጣት ይረዳል መባሉን ሞስኮ ታይምስ ዘግቧል።
ሀገራቱ ከሩሲያ የሚያስገቡትን የነዳጅ ዘይት ለማቆም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየመከሩ ሲሆን፥ ስለ እገዳው ዝርዝር ሁኔታ ግን መግለጫው ምንም ያለው ነገር የለም።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.