Fana: At a Speed of Life!

ከወረኢሉ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በተከሰተ አደጋ በ8 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደረሰ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከወረኢሉ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ ላይ በደረሰ የመገልበጥ አደጋ በስምንት ሰዎች ላይ ከባድ እና በ40 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደረሰ፡፡

የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሱ ዛሬ ከጠዋቱ 2 ሰአት አካባቢ በሰሜን ሸዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ ወርቄ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጨለሚት ከሚባለው ቦታ ነው የመገልበጥ አደጋ ያጋጠመው፡፡

በደረሰው አደጋም እስካሁን ባለው መረጃ 8 ከባድ የአካል ጉዳት በማጋጠሙ ለከፍተኛ ህክምና ወደ ሌላ ቦታ መላካቸውን የሚዳ ኦሮሞ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ከ40 በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል አደጋ ደርሶ በሚዳ ወረሞ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በህክምና ላይ ናቸው ተብሏል።

የአደጋውን መንስኤ ፖሊስ በማጣራት ላይ መሆኑን የሚዳ ወረሞ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር በላይነህ ሀይሉ ገልፀዋል ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.