Fana: At a Speed of Life!

ልዩነታችንን ተቀብለን ሀገራችንን ማፅናት አለብን – አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ልዩነታችንን ተቀብለን ሀገራችንን ማፅናት አለብን ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ተናገሩ።
ኢትዮጵያ እያሸነፈች ትሻገራለች በሚል መሪ ሃሳብ የፓናል ውይይት በጂግጂጋ ከተማ ተካሂዷል።
አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ልዩነታችንን ተቀብለን ሀገራችንን ማፅናት አለብን፤ ረጂም ታሪክ ያለን ሀገርና ሕዝብ መሆናችንን ለዓለም ለማሳየት ስለ ኢትዮጵያ ያገባኛል የሚሉ አካላት በእነዚህ መድረኮች ተገኝተው ሀገራችንን የሚጠቅሙ ሀሳቦች እንዲያካፍሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ÷ በሀገራዊ ጉዳይ ላይ የተዘጋጀው መድረክ ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ታዳሚዎች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡
በፓናል ውይይቱ ላይ በምሁራን የተዘጋጁ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደተደረገባቸው ኢዜአ ዘግቧል።
በመድረኩ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤትና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮችና አርቲስቶች እንዲሁም ጋራድ ኩልሚዬ ገራድ መሀመድ፣ ኦጋዞች፣ ሱልጣኖችናሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
በፓናል ውይይቱ ላይ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ያወያዩ ሲሆን÷ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳና አቶ አብረሃም አለኸኝ ፅሁፎችን አቅርበዋል።
ተመሳሳይ የፓናል ውይይቶች በ11 የክልል ከተሞች እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.