1ሺህ 33 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ የመመለስ ስራ 1ሺህ 33 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ከእነዚህ ውስጥ ስምንት ሕጻናት እንደሚገኙበት እና አጠቃላይ ከተመለሱት 1 ሺህ 25ቱ ወንዶች መሆናቸውን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡
እስካሁን በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ከ19 ሺህ 900 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል፡፡