የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ልዑክ ጎንደር ገባ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የልዑካን ቡድን ጎንደር ከተማ ገባ፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት አጼ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ÷ በክልል እና በከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
የሰባት ቤተ እምነት ተወካዮችን ያካተተው የልዑካን ቡድን በጎንደር በሚኖረው ቆይታ በከተማዋ በነበረው የፀጥታ ችግር ተጎድተው የነበሩ አከባቢዎችን ይጎበኛል።
በተጨማሪም በነገው ዕለት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያካተተ ውይይት እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡
በምናለ አየነው