Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ነዳጅ ዘይት ላይ የጣለው እገዳ የሞስኮን ገቢ ከፍ ሊደርግ ይችላል ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ነዳጅ ዘይት ላይ የጣለው እገዳ ሞስኮ በነዳጅ ዘይት የምታገኘውን ገቢ ይበልጥ ከፍ ሊያደርግ ይችላል የሚል እምነት እንዳላቸው አንድ የስዊዘርላንድ የምጣኔ ሀብት ተንታኝ ገለጹ፡፡

የስዊዘርላንዱ የምጣኔ ሀብት ተንታኝ ኖርበርት ራከር እንዳሉት÷በአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት የቀረበው የሩሲያ የነዳጅ ድፍድፍን ወደ አባል ሀገራቱ እንዳይገባ የመከልከል ሃሳብ የሞስኮን ገቢ ይበልጥ እንዲጨምር ከማድረግ ውጭ ፋይዳ የለውም ፡፡

ሩሲያ ላይ ለመጣል የታሰበው የነዳጅ ዘይት እገዳ አከራካሪ ጉዳይ መሆኑን ጠቁመው የአውሮፓ ህብረት ሞስኮን ማዳከም ከፈለገ ሌሎች የተሻሉ አማራጮችን ሊጠቀም ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

እገዳው ከታለመለት አላማ ባፈነገጠ መልኩ የዓለም ነዳጅ ድፍድፍ ዋጋ ይበልጥ እንዲያሻቅብ ከማድረግ በተጨማሪ ሩሲያ የነዳጅ ገቢዋ ከፍ እንዲል መልካም አጋጣሚ ሊፈጥርላት ይችላልም ነው ያሉት።

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የአውሮፓ ህብረት 27ቱም አባል ሀገራት የሩሲያን ነዳጅ ዘይት ወደ ሀገራቸው እንዳያስገቡ የሚከለክል እቅድ ማውጣቱን አር ቲ በዘገባው አስታውሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.