Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም የአምስተኛ ትውልድ የሞባይል ኔትዎርክን በይፋ አስተዋወቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም የአምስተኛ ትውልድ የሞባይል ኔትዎርክን በይፋ አስተዋወቀ።
ኢትዮ ቴሌኮም በአሁኑ ወቅት ዓለም የደረሰበትን አምስተኛ ትውልድ የሞባይል ኔትዎርክ (5ጂ) አገልግሎትን በይፋ አስተዋውቋል።
በምረቃ መርሃ ግብሩ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
አምስተኛ ትውልድ የሞባይል ኔትዎርክ በዓለም ዙሪያ ወደ ስራ የገባው በፈረንጆቹ 2019 ሲሆን ፥ በ2025 ላይም የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ ቁጥር 1 ነጥብ 7 ቢሊየን እንደሚደርስ ይገመታል።
አምስተኛ ትውልድ ኔትወርክ አገልግሎቱ ዛሬ በአዲስ አበባ የተጀመረ ሲሆን፥ በቀጣይ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።
የአምስተኛ ትውልድ ኔትወርክ ከቀደመው የአራተኛ ትውልድ አንጻር በ20 እጥፍ እንደሚበልጥ ተገልጿል።
በዱሬቲ ቶሎሳ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.