Fana: At a Speed of Life!

በጋሞ ዞን ከ68 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው ኮሌጅ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋሞ ዞን በ68 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የተገነባው የሰላምበር ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ተመረቀ፡፡
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ÷ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ሰልጣኞች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር ክህሎታቸውን በማሳደግ ወደ ተግባር እንዲቀይሩ የሚያግዙ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል፡፡
የሰላምበር ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅን ጨምሮ በዞኑ ውስጥ ስምንት ተቋማት አገልግሎት እየሰጡ መሆኑምን ጠቁመው÷ ቀሪ መስፈርት በሟሟላት ላይ ያሉ ኮሌጆችን ከክልሉ ጋር ተነጋግሮ በመክፈት ብቃት ያላቸውን ሰልጣኞች ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ኮሌጁ ያሉበትን ጉድለቶች እንዲያሟላ የጋሞ ዞን ከዘንድሮ በጀት 500 ሺህ እና ከቀጣይ በጀት ዓመት 1ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃልመግባቱን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.