Fana: At a Speed of Life!

የሰዎችን ክብር በሀሰት ለማጉደፍ በማህበራዊ የትስስር ገፅ ፎቶዎችን በመለጥፍ አፀያፊ ስድብ ያሰራጨው ተከሳሽ ተቀጣ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰዎችን ክብር እና መልካም ስም በሀሰት ለማጉደፍ በማሰብ በማህበራዊ ትስስር ገፅ ፎቶዎችን በመለጠፍ አፀያፊና አስነዋሪ ስድብ ያሰራጨው ተከሳሽ ተቀጣ፡፡
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተከሳሽ አብዮት አየለ በዛብህ ላይ የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈው፥ በተከፈተበት የክስ መዝገብ ላይ የኮምፒውተር ወንጀልን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ ላይ የተመለከተውን ህግ ተላልፎ በመገኘቱ ነው::
ተከሳሹ በ2012 እና 2013 ዓ.ም አምስት የተለያዩ የስራ ኃላፊዎችን ክብር እና መልካም ስም ለማጉደፍ በማሰብ (Abyot ayele) በማለት በከፈተው የፌስቡክ አካውንት ላይ የግል ተበዳዮችን ፎቶ በመለጠፍና አስነዋሪ ስድብ ጽፎ ያሰራጨ ሲሆን፥ በእዚህም በሰዎች ነጻነት እና ክብር ላይ በፈጸመው ወንጀል በሁለት መዝገብ ስምንት ክሶች እንደተመሰረተበት የድሬዳዋ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡
በእነዚህ ክሶችም የተከሳሹን ግለሰብ ተደጋጋሚ የወንጀለኝነት ባህሪ ጭምር በሚያስረዳ መልኩ የቀረበውን የክስ መዝገብ የተመለከተው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፥ ሚያዝያ 28 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ አብዮት አየለ በዛብህን በቀረቡበት ሁለት የክስ መዝገቦች ጥፋተኛ ሆኖ በማግኘቱ በአንድ አመት ከአምስት ወር እስራት እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱ ወስኖበታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.