Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል በአዲስ አበባ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም፣ የፍቅር፣ የመከባበር፣ የመቻቻል ተምሳሌት የሆነው የፊቼ ጨምበላላ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ሁነቶች ተከበረ።

የፊቼ ጨምበላላ በዓል ከዘመን መለወጫነቱ ባሻገር ከሰላም ተምሳሌትነቱ ከአቃፊነቱ አንጻር ለአንድነት የጎላ መሆኑ በበዓል አከባበር ላይ ተገልጿል።

የፊቼ ጨምበላላ በዓል የሰው ልጅ ለአከባቢ ጥበቃ እና ለእንስሳት ልዩ ስፍራ የሚሰጥም እንደሆነ ተመልክቷል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች መገኘታቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.