Fana: At a Speed of Life!

በባህሬን የኢፌዴሪ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ለመክፈት ዝግጅት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህሬን የኢፌዴሪ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ለመክፈት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራ የልኡካን ቡድን በሀገሪቱ የኢፌዴሪ የቆንስላ ጽህፈት ቤት መክፈት በሚቻልበት ገዳዮች ዙሪያ ለመምከር ባህሬን ገብቷል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት ባህሬን ሲደርሱም የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በኩዌት የኢፌዴሪ አምባሳደር አብዱልፋታህ ሃሰን እና በባህሬን የኢፌዴሪ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ተወካይ ወይዘሮ እስከዳር ግርማይ አቀባበ አድርገውላቸዋል።

ቆንስላ ጽህፈት ቤቱ የሚከፈተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመካከለኛ ምስራቅ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በቅርቡ በዱባይ ውይይት በሰጡት አቅጣጫ መሰረት ነው ተብሏል።

ቡድኑ በቆይታው በባህሬን ከሚኖሩ የተለያዩ የማህበረሰብ አባላት ጋር በጋራና በተናጠል በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ የሚወያይ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከዚህ ባለፈም ከባህሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ጋር በባህሬን ያሉ ዜጎችን መብት፣ጥቅም እና ደህንነት በሚጠበቅበት ዙሪያ የሚመክር ይሆናል።

በተጨማሪም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.