Fana: At a Speed of Life!

በወሊድ ወቅት በአምቡላንስ እጦት የተሰቃዩት እናት የ12 ሚሊየን ብር አምቡላንስ አበረከቱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘዲቱ ሆስፒታል ፋርማሲስት የሆኑት ወይዘሮ ሃና ልካስ ለሆስፒታሉ ዘመናዊ የአንቡላንስ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ግለሰቧ ያደረጉት የአምቡላንሶ ድጋፍ በገንዘብ ሲተመን ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ሲሆን፥ በተለይ ለእርጉዝና ላይ ያሉ እናቶች አስፈላጊውን የህክምና ድጋፍ እያገኙ ወደ ሆስፒታል እንዲደርሱ እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡
አምቡላንሱ ዘመናዊ የመተንፈሻ ቬንትሌተር የተገጠመለት ሲሆን በተለይ እናቶች አምቡላንሱ ላይ የመውለድ እድል ቢገጥማቸው እንኳ ሙሉ ድጋፍ ማግኘት ያስቸላል ተብሏል።
ድጋፉን ያደረጉት ወይዘሮ ሃና ከዚህ ቀደም ለመውለድ ወደ ሆስፒታል በሚሄዱበት ወቅት አምቡላንስ ባለማግኘታቸው በማይመች መኪና ወደ ሆስፒታል በመሄዳቸው ችግር እንደገጠማቸው ገልጸው፥ ከራሳቸው ተሞክሮ በመነሳት ሌሎች እናቶች ተመሳሳይ ችግር እንዳይደርስባቸው የሚያግዝ አምቡላንስ ከሀገር ውጭ ከሚገኙ ወዳጆቻቸው ጋር በመተጋገዝ ድጋፉን እንዳደረጉ አስረድተዋሠዋል።
እያንዳንዱ ሰው የሚችለውን አስተዋፅኦ ቢያደርግ በሀገራችን ያሉ ችግሮች ይፈታሉ የሚሉት ወይዘሮ ሃና፥ በተለይም በሀገራችን የገጠሩ ክፍል ለሚገኙ እናቶች በወሊድ ጊዜ የሚያጋጥማቸውን የህክምና እጦት መቅረፍ ይቻላል ነው ያሉት።
ድጋፉን የተረከቡት የዘውዲቱ ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ዘላለም ጭምዴሳ በበኩላቸው÷ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው ድጋፉ ብዙ ችግር እንደሚቀርፍ ተናግረዋል።
በዓለምሰገድ አሳዬ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.