Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል በተካሄደ ዘመቻ አሸባሪው አል-ሸባብ በድንበር አከባቢ የቀበረው በርካታ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል እና የመረጃና ደህንነት አገልግሎት አካላት ባደረጉት የጋራ ዘመቻ አሸባሪው አል-ሸባብ በድንበር አካባቢ የቀበረው በርካታ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ሥር ዋለ፡፡
በሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ከሶማሊያ ድንበር አካባቢ የተሰማሩ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አባላት እና የመረጃ አካላት÷ በባረይ ወረዳ በደዊ ቀበሌ አሸባሪው አል-ሸባብ ያከማቸው በርካታ የጦር መሳሪያ ከ8 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር አውለዋል፡፡
በዘመቻው÷ 50 AK 47 ወይም ክላሽን ኮቭ፣ 10 RPG መሳሪያዎችና ከ50 በላይ ሽጉጦች እንዲሁም በርካታ ጥይቶች መያዛቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
አሸባሪው አል-ሸባብ በሁለቱ ሀገራት ድንበር ላይ የደበቀው የጦር መሳሪያ የሽብር ጥቃቶች ሊፈጸምባቸው እንደነበርም ነው የተመላከተው፡፡
ዒላማ የተደረጉ አከባቢዎችም ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.