ስፓርት

አትሌት ፀሐይ ገመቹ በሊዝበን ግማሽ ማራቶን ድል ተቀዳጀች

By Meseret Awoke

May 10, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) አትሌት ፀሐይ ገመቹ በፖርቹጋል ዋና ከተማ ሊዝበን በተካሄደው የግመሽ ማራቶን ውድድር ለሁለተኛ ጊዜ አሸነፈች፡፡

አትሌቷ የሊዝበንን ግማሽ ማራቶን ርቀት 1 ሰዓት ከ06 ደቂቃ ከ44 ሴኮንድ በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቅቃለች፡፡

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጎይተይቶም ገብረ ስላሴ 1 ሰዓት ከ06 ደቂቃ 45 ሴኮንድ በመግባት 3ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡