Fana: At a Speed of Life!

ታይዋንን በተመለከተ አሜሪካ እውነታን እያዛባች ነው ስትል ቻይና ክፉኛ ወቀሰች

አዲስ አበባ፣ግንቦት 2፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ታይዋንን በተመለከተ ዩናይትድ ስቴትስ እውነታን እያዛባች ነው ስትል ቻይና ክፉኛ ወቀሰች።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስ ታይዋንን በተመለከተ እያወጣች ያለችው መረጃ የተዛባ መሆኑን በመግለፅ ዋሽንግተን ቀደም ሲል ስትገዛለት ለነበረው ለአንድ ቻይና ፖሊሲ ዛሬም እንድትቆም አሳስቧል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በፈረንጆቹ ግንቦት 5 አሻሽሎ ባወጣው ሰነድ ላይ ታይዋን የቻይና አካል ናት የሚለውንና አሜሪካ የታይዋንን ነፃ ሀገር መሆንን አትደግፍም የሚሉትን አንቀጾች ማጥፈቱን የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ዣኦ ሊጂያን በመደበኛ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ እንደተናገሩት፥ የአሜሪካው የቅርብ ጊዜ ድርጊት የአንድ ቻይናን መርህን ለማጥፋት መሆኑን አመላክተዋል፡፡
የታይዋን ሰርጥን በተመለከተ በሚፈፀም እንዲህ ዓይነት የፖለቲካ ሸፍጥ ውስጥ የሚገኙ በእሳት እየተጫወቱ ያሉ ይቃጠላሉ ሲል ቃል አቀባዩ አስጠንቅቋል፡፡
ቃል አቀባዩ “ አንዲት ቻይና አለች፤ ታይዋንም የማትነጠል የቻይና ግዛት ናት፤ የቻይና መንግስት ሁሉንም የቻይና ግዛት በዓለም መድረክ ይወክላል” ብለዋል በመግለጫቸው።
ይህ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በስፋት የሚደግፈው እና ዓለም አቀፍ ግንኙነትን የሚገዛ እውነታ መሆኑንም ጠቁመዋል።
እንደ ሲ ጅ ቲ ኤን ዘገባ ባለፈው ህዳር ወር ላይ የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ እና የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በስልክ ባደረጉት ውይይት ዋኝንግተን የታይዋንን ነፃ ሀገር መሆኑን እንደማትደግፍ ባይደን አረጋግጠው ነበር።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.