Fana: At a Speed of Life!

ዩን ሱክ ዮል አዲሱ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት በመሆን ቃለ መሃላ ፈጸሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩን ሱክ ዮል አዲሱ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት በመሆን በሀገሪቱ ዋና ከተማ ሴኦል በሚገኘው ብሄራዊ ምክር ቤት ቃለ መሃላ ፈፀሙ።

ፕሬዚዳንቱ በቀጣይ አምስት አመታት በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ በቃለ መሃላ ስነ ስርዓቱ ላይ፥ ፒዮንግያንግ የኮሪያ ልሳነ ምድርን ከኑክሌር ጦር መሳሪያ ነፃ ለማድረግ ከልቧ ከሰራች ሀገራቸው ከቀሪው ዓለም ጋር በመሆኑን የሰሜን ኮሪያ ኢኮኖሚ የሚያጠናክር እና የህዝቦቿን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሽል እቅድ እንደምታዘጋጅ ቃል ገብትዋል።

የሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር መርሃ ግብር ለሀገራቸው ብቻ ሳይሆን ለሰሜን ምስራቅ እስያም ጭምር ስጋት መሆኑን ያነሱት አዲሱ ፕሬዚዳንት፥ ለሰላማዊ መፍትሄና ድርድር ግን በራቸው ክፍት መሆኑን ጠቁመዋል።

ፕሬዚዳንቱ በሀገራቸው እና በሰሜን ኮሪያ መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ ይረዳቸው ዘንድ ሴኦል ከቤጂንግ ጋር ያላትን ግንኙነት ማስተካከል ይጠበቅባቸዋል።

ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ሙን ጃ ኢን በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል ሲካሄድ የነበረው ውይይት እንደገና እንዲጀመር ባለፈው ሰኞ ጥሪ ማቅረባቸውን የአናዱሉ ዘገባ አስታውሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.