Fana: At a Speed of Life!

ፔፕፋር በኢትዮጵያ ኤች አይ ቪን ለመከላከል የሚውል የ106 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፔፕፋር በኢትዮጵያ ኤች አይ ቪ /ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚውል የ106 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አፀደቀ።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለኤች አይ ቪ/ኤድስ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመርዳት በአሜሪካ የተቋቋመው ፔፕፋር መርሃ ግብር አመራሮች በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
በጉብኝታቸውም ከጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ እና ከሌሎች የሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር ተወያይተዋል፡፡
መርሃ ግብሩ በኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት ኤች አይ ቪ/ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚውል የ106 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ማጽደቁን በኢትዮጵያ ከአሜሪካ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ፔፕፋር በኢትዮጵያ ቫይረሱን ለመከላከል ከዩ ኤስ ኤይድ ፣ ከጤና ሚኒስቴር እና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በቅንጅ እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.