Fana: At a Speed of Life!

ሃዋሳ ከተማ እና ስሑል ሽረ ከአሰልጣኞቻቸው ጋር ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሁለቱ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቡድኖች ሃዋሳ ከተማ እና ስሑል ሽረ ከአሰልጣኞቻቸው ጋር ተለያይተዋል።

የሃዋሳ ከተማ ቦርድ የቡድኑን የቀድሞ አሰልጣኝ አዲሴ ካሳን በማንሳት ብርሃኑ ወርቁን በጊዚያዊ አሰልጣኝነት መሾሙን ከሶከር ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ ቡድኑ በፕሪሚየር ሊጉ 15ተኛ ሳምንት ከፋሲል ከነማን አስተናግዶ 3 ለ 2 ካሸነፈ በኋላ ለሳምንት ወደ ቡድኑ እንዳልተመለሱ ተጠቁሟል።

ይህን ተከትሎም ቦርዱ ባደረገው ስብሰባ አሰልጣኙን በማሰናበት የሀዋሳን ከ20 ዓመት በታች አሰልጣኝ የነበሩትን ብርሃኑ ወርቁን በጊዜያዊነት ሾሟል።

በተያያዘ ዜና ባለፈው ሳምንት የመልቀቂያ ደብዳቤ ያስገቡት የስሑል ሽረ አሰላጣኝ ሳምሶን አየለ ከቡድኑ ጋር ተለያይተዋል፡፡

ለአንድ ዓመት ያክል ከቡድኑ ጋር ቆይታ የነበራቸው አሰልጣኙ በግል ምክንያንት ቡድኑን እንደለቀቁ ታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.