Fana: At a Speed of Life!

አምስተኛው የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምስተኛው የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

“የለውጥ ማዕበል በነገሰበት ዘመን የነገውን የፋይናንስ ዘርፍ እንደገና መቅረጽ” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ያለው ጉባኤ፥ ፖሊሲዎችን እና አሰራሮችን መፈተሽ እንዲሁም የፋይናንስ ዘርፉን የወደፊት አቅጣጫ መቀየስ፣ ህግና ደንብን የማጥራት ዓላማዎች መያዙ ተገልጿል።

በጉባኤው ጠንካራ የፋይናንስ ዘርፍ እንዲፈጠር የሚያስፈልገው ፖሊሲ፣ ቁጥጥርና አስተዳደር፣ የፋይናንስ አካታችነትና ልዩ የባንክ አገልግሎቶችን በተመለከተ ውይይት እየተደረገ ሲሆን በጉባኤው በፋይናንስ ሥርዓቱ ላይ የተለያዩ ጥናቶች እንደሚቀርቡና የፋይናንስ ሥርዓት ፖሊሲ በስፋት እንደሚገመግም ይጠበቃል።

የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባኤ በየአመቱ የሚካሄድ ሲሆን÷ የዘንድሮ አምስተኛውን የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባኤ አይ ካፒታል አፍሪካ ኢኒስቲቲዩት፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ መድን ሰጪዎች ማህበርና የተመሰከረላቸው የሂሳብና ኦዲት ባለሙያዎች ማህበር በጋራ አዘጋጅተውታል።

በጉባኤው የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴን ጨምሮ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች፣ የቴክኖሎጂ አቅራቢዎችና በምስራቅ አፍሪካና በውጭ የሚገኙ ቁልፍ የፋይናንስ ተቋማት ተገኝተዋል።

በታሪኩ ለገሰ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.