የዩክሬን የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ሊዮኒድ ክራቭቹክ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩክሬን የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ሊዮኒድ ክራቭቹክ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰማ።
ክራቭቹክ ባደረባቸው ህመም ሳቢያ በ88 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ፕሬዚዳንቱ ለረጅም ጊዜ በልብ ህመም ሳቢያ ህክምና ሲከታተሉ መቆየታቸውን ቤተሰቦቻቸው ለዩክሬን ዜና አገልግሎት ገልጸዋል፡፡
በምዕራባዊው የዩክሬን ክፍል ሮቭኖ ከተማ የተወለዱት ፕሬዚዳንት ክራቭቹክ በፈረንጆቹ ነሐሴ 1991 የዩክሬን ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት በመሆን እና የዩክሬን ህገመንግስት ከጸደቀ በኋላ ደግሞ ታህሳስ 5 ቀን 1991 የሀገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ተብለው መመረጣቸው ተገልጿል፡፡
ክራቭቹክ በፈረንጆቹ 1994 በሊዮኒድ ኩችማ በድጋሚ ምርጫ ተወዳድረው መሸነፋቸውን አርቲ ዘግቧል።