Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ድሬዳዋ ከተማ ሀዲያ ሆሳዕናን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ23ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ ሀዲያ ሆሳዕናን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸንፏል፡፡
 
ረፋድ 4 ሰዓት በተደረገው ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ ሀዲያ ሆሳዕናን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ ወሳኝ 3 ነጥብ ከባህርዳር ስታዲየም ማግኘት ችሏል፡፡
 
ለድሬዳዋ ከተማ ሄኖክ አየለ እና አብዱራህማን ሙባረክ ሁለት ሁለት ጎሎችን በስማቸው ማሰቆጠርችለዋል፡፡
 
ድሬዳዋ ዛሬ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 27 በማድረስ ከወራጅ ቀጠና ስጋት መውጣት ሲችል÷ሃዲያ ሆሳዕና ወደ 6ኛ ደረጃ የሚመጣበትን እድል አምክኗል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.