Fana: At a Speed of Life!

ኮይካ እና ሰላም ሚኒስቴር ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ማህበረሰብ አቀፍ መፍትሄዎችን ለማጠናከር የሚያሰራ ፕሮጀክትን ለመፈፀም ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) እና የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ማህበረሰብ አቀፍ መፍትሄዎችን ለማጠናከር የሚሰራ ፕሮጀክትን ለመፈፀም ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
 
ፕሮጀክቱ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ዘላቂ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋትን መፍጠር የሚያስችሉ ማህበረሰብ አቀፍ የሰላም መፍትሄዎችን ለማበረታታት ያለመ ነው ተብሏል፡፡
 
ፕሮጀክቱ በፈረንጆቹ ከ2022 እስከ 2025 የሚተገበር ሲሆን፥ ለዚህም 10 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የተመደበ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
መርሃ ግብሩ በኦሮሚያ ክልል 5 ወረዳዎች እና በሶማሌ ክልል 5 ወረዳዎች የሚተገበር መሆኑንም ኮይካ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.