በሱሉልታ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 45 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ተያዘ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱሉልታ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 45 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ተያዘ፡፡
የጦር መሳሪያው ከጋምቤላ ክልል በመነሳት አዲስ አበባን አልፎ ወደ ባህርዳር ሊጓዝ ሲል ነው በሱሉልታ ከተማ የተያዘው፡፡
የሱሉልታ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ዳይሬክተር ኮማንደር ነገሪ ዲባ÷33 ባለ ሰደፍ እና 12 ታጣፊ ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች የጸጥታ አካላት ባደረጉት ክትትል እንደተያዘ መናገራቸውን ከከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡