Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ የሲሚንቶ ፋብሪካ ሃላፊዎች ጋር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ከሚንቀሳቀሱ የሲሚንቶ ፋብሪካ ሃላፊዎች ጋር የሲሚንቶ ግብዓት አቅርቦት እና ፋብሪካዎች በሚገኙባቸው አካባቢዎች ስላለው የፀጥታ ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡
በውይይቱ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጅነር ታከለ ኡማ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ እንዲሁም በክልሉ የሚገኙ የሲሚንቶ ፋብሪካ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡
ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት÷“በውይይታችን የሲሚንቶ ግብዓት አቅርቦት እና ፋብሪካዎቹ በሚገኙባቸው አካባቢዎች ስላለው የፀጥታ ሁኔታ ላይ ተነጋግረናል” ብለዋል፡፡
ወጣቶችን ከፋብሪካዎቹ ጋር በማስተሳሰር የስራ እድል ማግኘት የሚችሉበትን መንገድ ለማመቻቸትም ስምምነት ላይ መደረሱን ጠቁመዋል፡፡
የአካባቢው ወጣቶች በዘርፉ ላይ ያላቸውን ተጠቃሚነት ማስከበር የወጣቶች ህይወት የሚያሻሽል ሲሆን÷በተጨማሪም ማህበረሰቡ በአካባቢው ለሚገኙ ተቋማት የሚኖሮውን የኔነት ስሜት የሚያሳድግ ነው ብለዋል፡፡
ይህም ለአካባቢው ሰላም እና ፋብሪካዎቹ የሚገጥማቸውን ችግር ለማስቀረት የጎላ ሚና እንደሚኖረው ተግባብተናል ነው ያሉት ሚኒስትሩ።
በሲሚንቶ ግብይት ስርዓቱ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታትም በቅንጅት ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱንም ተናግረዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.