የኢትዮጵያ ከተሞች ከንቲባዎች በደቡብ አፍሪካ የልምድ ልውውጥ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከተሞች ማህበር እና ከተለያዩ ከተሞች የተወጣጡ ካንቲባዎች ከደቡብ አፍሪካ አቻ ማህበራት ጋር የልምድ ልውውጥ አድርገዋል።
በልምድ ልውውጡ በኢትዮጵያ ከተሞች ማህበር አስተባባሪነት የሐዋሳ፣ አዳማ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ጅግጅጋ፣ ይርጋለም ከተሞች ከንቲባዎች እና የሲዳማ ክልል ከተማ ልማት ምክትል ቢሮ ኃላፊ ተሳትፈዋል።
የልምድ ልውውጥ በከተሞች አቅም ግንባታ ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የልዑካን ቡድን አባላቱ በቆይታቸው ከኤምባሲው ዲፕሎማቶች ጋር የከተሞችን የጉድኝት ስራዎች መልክ በያዘ መንገድ በትብብር ለመስራት መስማማታቸው ተገልጿል።