Fana: At a Speed of Life!

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ማዕከል የማስጀመሪያ መርሃግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ማዕከል የማስጀመሪያ መርሃግብር በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።

በመርሃግብሩ ማስጀመሪያ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት አባላት መምህራን፣ ተማሪዎች እና አመራሮች ተሳትፈዋል::

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳድር ዲና ሙፍቲ ዩኒቨርሲቲው በግብርናው ዘርፍ ለሀገር ችግር ፈቺ የምርምር ውጤቶችን እያበረከት አመታትን የዘለቀ ነው ብለዋል::

ዩኒቨርሲቲው አሁን ላይ በግብርናው ዘርፍ ከሚያበረክተው አስተዋፅኦ ባለፈ ከውጭ ያሉ የተለያዩ ጫናዎችን ለመቋቋም ሀገሪቷ ከአንጋፋው ዩኒቨርሲቲ ብዙ ነገር ትጠብቃለች ለዚህም ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ወቅቱ የሚፈልገውን አማራጭ በመጠቀምም ብሄራዊ ጥቅምን ማስከበር እና ለሀገር ሉአላዊነት ዘብ መቆም እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል።

መርሀግብሩ በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን ጨምሮ ብሔራዊ ጥቅሞች ላይ ሁሉም ዜጎች በፐብሊክ ዲፕሎማሲ ለሀገራቸው እንዴት መሞገት እና ተጽዕኖ ማሳደር እንደሚችሉ ተማሪዎችን ማብቃት እንደሚገባም ተናግረዋል።

በአዲሱ ሙሉነህ እና ተሾመ ሃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.