Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ቡና በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ 1 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ አስገኘ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቡና በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ 1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሪ አስገኘ።
የኢፌዴሪ የግብርና ሚኒስትር ኡመር ሁሴን ለዚህ ታሪካዊ ላሉት ስኬት እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።
የቡና ምርት ኢትዮጵያ ለዓለም ገበያ ከምታቀርባቸው የግብርና ምርቶች መካከል ግንባር ቀደም ሆኖ ቀጥሏል።
ሀገሪቱ በተለይም ወደ ቻይና የምትልከው የቡና ምርት በከፍተኛ መጠን አድጓል።
በፈረንጆቹ 2021 ዓመተ ምህረት ላይ ቻይና ከኢትዮጵያ ያስገባቸው የቡና ምርት መጠን ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ196 በመቶ አድጓል።
በቅርቡ የኢትዮጵያን የቡና ምርት በቻይና ገበያ የበለጠ ለማስተዋወቅ በተዘጋጀ መድረክ ላይ የሀገሪቱ የቡና ማህበር እንዳስታወቀው፥ በቻይና ከትላልቅ ከተሞች እስከ መለስተኛ ከተሞች የቡና ተጠቃሚዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ ዕድገት ያሳየ ሲሆን፥ ይህም ለኢትዮጵያ ቡና አምራቾች እና ላኪዎች ሰፊ የገበያ ዕድል መፈጠሩ ተመልክቷል።
ሚኒስትሩ ባለፉት የበጀት ዓመቱ ወራት የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ምን ያህል የቡና መጠን ወደ ውጭ ተልኮ እንደሆነ አልጠቆሙም።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.