የሀገር ውስጥ ዜና

ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ በጂንካ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው

By Meseret Awoke

May 12, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ”የጥናትና የምርምር ስራዎች ለዕውቀት ሽግግርና ለዘላቂ ልማት” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው አራተኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ በጂንካ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ይገኛል።

በኮንፈረንሱ በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማቶች ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች እንደሚቀርቡ ተገልጿል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው የምርምር ኮንፍረንሱ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢና የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ፣ የቦርዱ አባላት ፣የደቡብ ክልልና ደቡብ ኦሞ ዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ምሁራን እየተሳተፉ ነው።

ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ ጥናት አቅራቢዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እንደተገኙም ኢዜአ ዘግቧል።