ዓለም አቀፉ ጥምረት በአፍሪካ ጽንፈኛ ቡድኖችን ለመዋጋት የሚያደርገውን ጥረት እንደሚቀጥል አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ግንቦት 4፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ዓለም አቀፉ ጥምረት በአፍሪካ ጽንፈኛ ቡድኖችን ለመዋጋት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡
ከ60 በላይ አጋሮች ያሉት የዓለም አቀፉ ጥምረት ቡድን በሞሮኮዋ ማራካሽ ከተማ ባካሄደው ስብሰባ አይ ኤስን ጨምሮ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ጽንፈኛና አክራሪ ቡድኖችን ለማጥፋት የሚያደርገውን ጦርነት እንደሚቀጥል ቃል ገብቷል፡፡
የሞሮከው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናስር ቦሪታ በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት በአፍሪካ ያለውን አደገኛ የሽብርተኝነት ስጋት በተመለከተ ያደረግነው ውይይት ለአፍሪካ አህጉር ከፍተኛ ፋይዳ አለው ብለዋል፡፡
በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖለቲካ ጉዳዮች ፀሃፊ ቪክቶር ኑላንድ በበኩላቸው አሜሪካ የሽብር ቡድኖችን ለማጥፋት ከምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ጋር በጋራ ትስራለች ብለዋል፡፡
ጠንካራ መንግስት አለመኖር፣ የመብት ጥሰቶች እና የምግብ ዋስትና እጦት ለአሽባሪዎች መስፋፋት ምክንት መሆናቸውንም ቪክቶር ኑላንድ ጠቁመዋል፡፡
ዓለም አቀፉ ጥምረት ቡድን በፈረንጆቹ 2014 የተመሰረተ ሲሆን 84 ሀገራትንና እና ዓለም አቀፍ ተቋማትን አካቷል ።
የአሜሪካ ፀረ-ሽብር ቢሮ ባወጣው መራጃ በሳህል ቀጠና ከፈረንጆቹ 2018 እስከ 2021 ባሉት ጊዜያት የሽብር ጥቃት በ43 በመቶ መጨመሩን አፍሪካ ኒውስ በዘገባው አስታውሷል።