Fana: At a Speed of Life!

የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችን ጫና የሚመከተው የሀገርንና የህዝብን ክብር በመጠበቅ ሀገር በቀል ተኪ ምርቶችን በማምረት መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 4፣2014 (ኤፍ ቢሲ) አዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ 11ኛ ዙር ተመራቂ ኢንተርፕራይዞች በከተማዋ ያሉ ውጤታማ ባለሀብቶችና ተቋማት በተገኙበት ውይይት እያደረጉ ነው።
የውይይቱ አላማ ተመራቂ ኢንተርፕራይዞች ወደ መካከለኛ ኢንዱስትሪ ሲሸጋገሩ የሚጠብቃቸውን ሚና ተረድተው ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል እንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገልፀዋል።
እንደ አቶ ጃንጥራር ገለፃ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በከተማዋ የሚገኙ 36 ሺህ በላይ ኢንትርፕራይዞችና ኢንዱስትሪዎችን ከ90 ሺህ በላይ አንቀሳቃሽ አቅፈው የከተማዋን የምጣኔ ሀብት እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ከፍተኛ አሰተዋፆ እያበረከቱ ይገኛሉ።
የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የኢንተርኘራይዞች ድጋፍ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ፍስሃ ጥበቡ በበኩላቸው፥ ኢንተርፕታይዞችን ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረግ አቅማችውን የማሳደግ፣ የምርት ጥራትና የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማስቻል የእድገት ደረጃ ሽግግር በማከናወን ከጥቃቅን ጀማሪ እስከ መካከለኛ ኢንዱስትሪ እንዲሸጋገሩ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
በዚህ ዓመት 179 ኢንተርፕራይዞች መስፈረቱን ያሟሉና ወደ ከፍተኛ ኢንዱስትሪ የሚሸጋገሩትን የማስመረቅ ስራ እንደሚከናወን በመድረኩ መገለፁን ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.