Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ቀንሶ የነበረው የወባ በሽታ ዳግም በስፋት እየታየ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ከዚህ በፊት ቀንሶ የነበረው የወባ በሽታ በአሁኑ ወቅት ዳግም በስፋት መታየቱን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለፀ።

የቢሮው የህዝብ ግንኙነትና ጤና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ቀድራላህ አህመድ እንዳሉት፥ በክልሉ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ ያለውን የወባ በሽታ ለመከላከል ህብረተሰቡ ትኩረት እንዲሰጥ የክልሉ ጠና ቢሮ አሳስቧል።

በክልሉ በላብራቶሪ በተደረገ ምርመራ ከ242 ሺህ በላይ ሰዎች ወባ ተገኝቶባቸው ህክምና መውሰዳቸው ተገልጿል።

ዳይሬክተሩ ይህም በክልሉ ከዚህ በፊት ቀንሶና የነበረው የወባ በሽታ በአሁኑ ወቅት ዳግም እየተስፋፋ ለመሆኑ መሳያ መሆኑን ጠቁመዋል።

ቢሮው በሽታውን ለመከላከል 1 ነጥብ 2 ሚሊየን አጎበሮችን በ31 ወረዳዎች ለማከፋፈል እየሰራ መሆኑንና የኬሚካል እርጭትም በተቀናጀ መንገድ እያካሄደ መሆኑን አቶ ቀድራላህ ገልጸዋል፡፡

ክረምት እየደረሰ በመሆኑ የበሽታው ስርጭቱ የከፋ እንዳይሆን ህብረተሰቡ ያቆሩ ውሃዎችን የማፋሰስ፣ የማዳፈንና አጎበር በአግባቡ በመጠቀም እንዲሁም የበሽታ ምልክቶች ሲታዩ የአስቸኳይ ህክምና በመውሰድ በሽታውን ለመከላከል በሚደርገው ጥረት የድርሻቸውን እንዲወጡ ቢሮው አሳስቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.