Fana: At a Speed of Life!

በዳኝነት ስርዓቱ ላይ የሚታዩ የሙስና ተግባራትን ለመከላከል የሚያስችል ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዳኝነት ስርዓቱ ላይ የሚታዩ የሙስና ተግባራትን ለመከላከል የሚያስችል ስትራቴጂ ይፋ አደረገ።

በስትራቴጂው ፋይዳ እና በቀጣይ አተገባበሩ ዙሪያ በማተኮር ከዳኞችና ከሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መዓዛ አሸናፊ÷ በፍትህ አሰጣጥ ሂደት የትውውቅ አሰራር፣ ጉቦና የመሳሰሉት ብልሹ አሰራሮች ፈተና እየሆኑ መምጣታቸውን ገልጸዋል።

የዳኞች አገልግሎት አሰጣጥ ከሙስና ተግባር የፀዳ መሆን እንዳለበት ጠቅሰው÷ አንዳንድ ዳኞች፣ የጉባኤ ተሿሚዎችና የፍርድ ቤት ሰራተኞች በሙስና ፍትሕ እንዲዛባ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.