Fana: At a Speed of Life!

በህገ- ወጥ መንገድ 7 ሕፃናቶችን ሲያዘዋውር የተገኘው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በህገ- ወጥ መንገድ ሰባት ሕፃናቶችን ሲያዘዋውር የተገኘው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

ፖሊስ እንዳስታወቀው፥ ተጠርጣሪው ግለሰብ ከካፋ ዞን ጨና ወረዳ ባላ ሻሻ ቀበሌ ከአስር ዓመት በታች የሆኑ ሰባት ሕፃናቶችን ከሚኖሩበት ቤተሰብ ከብቶችን ትጠብቃላችሁ በማለት ወደ ቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ ጉፍቃ ቀበሌ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠዋቱ 3:00 በተሽከርካሪ ህፃናቶቹን ይዞ በመጓዝ ላይ እንዳለ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆኖ ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል።

ህብረተሰቡ ህፃናቶች በህገወጥ መንገድ ከቦታ ወደቦታ እያዘዋወሩ ለጉልበት ብዝበዛ የሚዳርጉ ግለሰቦችን ለህግ አካላት አሳልፎ መስጠት እንዳለበትም ፖሊስ ማሳሰቡን ከደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.