የሀገር ውስጥ ዜና

በህገ- ወጥ መንገድ 7 ሕፃናቶችን ሲያዘዋውር የተገኘው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

By Feven Bishaw

May 12, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በህገ- ወጥ መንገድ ሰባት ሕፃናቶችን ሲያዘዋውር የተገኘው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

ፖሊስ እንዳስታወቀው፥ ተጠርጣሪው ግለሰብ ከካፋ ዞን ጨና ወረዳ ባላ ሻሻ ቀበሌ ከአስር ዓመት በታች የሆኑ ሰባት ሕፃናቶችን ከሚኖሩበት ቤተሰብ ከብቶችን ትጠብቃላችሁ በማለት ወደ ቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ ጉፍቃ ቀበሌ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠዋቱ 3:00 በተሽከርካሪ ህፃናቶቹን ይዞ በመጓዝ ላይ እንዳለ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆኖ ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል።