Fana: At a Speed of Life!

አቶ መላኩ አለበል ከሶፍሌት ማልታ ኢትዮጵያ ሼር ካምፓኒ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 4፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ከሶፍሌት ማልታ ኢትዮጵያ ሼር ካምፓኒ ስራ አስኪያጅ ጃን ቦንት ቪቬት ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል÷ ብቅል አማራች ካምፓኒው ሶፍሌት ማልታ በኢትዮጵያ እደረገ ያለውን ጥሩ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በመገንዘብ ሚኒስቴር መስሪ ቤቱ ለድርጅቱ የኢንቨስትመንት እገዛ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡

የሶፍሌት ማልታ ጀነራል ማናጀር ጃን ቦንት ቪቬት በበኩላቸው÷ 60 ሚሊየን ዩሮ ኢንቨስት በማድረግ ከውጪ የሚገባውን የምርት ግብዓት ለመቀነስ ከአርሶአደር ማህበረሰብ ጋር ትስስር በመፍጠር ጥሬ ዕቃዎችን ለማግኘት ዘመናዊ አሰራር ተግባራዊ እያደረጉ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የቢራ ፋብሪካዎችን የብቅል ፍላጎትን ለመሙላት ሶፍሌት ማልታ ኢትዮጵያ ሼር ካምፓኒ በዓመት ከውጪ ከሚገባው ብቅል 50 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያድንም መግለፃቸውን ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.