የሀገር ውስጥ ዜና

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ጅግጅጋ ገቡ

By Feven Bishaw

May 13, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ እና የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ እና ልዑካቸው ጅግጅጋ ከተማ ሲደርስ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶች እና ኡጋሶች ደማቅ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከአፋር ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።