Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የግብፅ አቻውን በማላዊ ቢንጉ ስታዲየም ያስተናግዳል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከግብፅ አቻው ጋር የሚያደርገው ጨዋታ በማላዊ ቢንጉ ስታዲየም እንዲካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ወስኗል፡፡

ቀደም ሲል ለኢንተርናሽናል ጨዋታዎች የተመረጠው የባህርዳር ስታዲየም የካፍ ደረጃን ባለማሟላቱ ካፍ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምታደርገውን ጨዋታ በሌላ ሀገር ስታዲየም እንድታደርግ መወሰኑ የሚታወስ ነው፡፡

በመሆኑም ካፍ ኢትዮጵያ የማጣሪያ ጨዋታዋን የምታደርግበትን ስታዲየም እንድታሳውቅ መጠየቁን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከግብፅ አቻው ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ የሚጫወትበትን ስታዲም አሳውቋል፡፡

በዚህም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የግብፅ አቻውን በቀድሞው የማላዊ ፕሬዝዳንት ቢንጉ ዋ ሙታሪካ ስም በተሰየመው ቢንጉ ስታዲየም ጨዋታውን እንደሚያደርግ ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የማላዊ የቢንጉ ብሔራዊ ስታዲየም 41 ሺህ 100 ተመልካች የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን፥ በአውሮፓውያኑ በ2017 ግንባታው ተጠናቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.