Fana: At a Speed of Life!

ፊንላንድ ኔቶን የምትቀላቀል ከሆነ ሩሲያ አጸፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ አስታወቀች

አዲስ አበባ ፣ግንቦት 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ጎረቤቷ ፊንላንድ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶን) ለመቀላቀል የምታደርገውን ጥረት የምትቀጥል ከሆነ አጸፋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለች።
 
የፊንላንድ ፕሬዚዳንት ሳውሊ ኒኒስቶ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳና ማሪን ትናንት በጋራ ባሰጡት መግለጫ÷ ፊላንድ የኔቶ አባል እንድትሆን መወሰኗን እና ለዚህም አስፈላጊው ሂደት በፍጥነት መጀመር እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
 
የፊንላንድን ውሳኔ ተከትሎ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት÷ ፊንላንድ ኔቶን ለመቀላቀል የጀመረችው እንቅስቃሴ ግልጽ ጠብ አጫሪነት ነው፡፡
 
እንቅስቃሴው የሁለቱን አገራት ግንኙነት ይበልጥ ከማሻከሩ ባለፈ በሰሜን አውሮፓ የሚስተዋለውን አለመረጋጋት ይበልጥ እንደሚያባብሰውም አመላክተዋል፡፡
 
ስለሆነም ሩሲያ ከድርጊቱ የሚመነጭን ማንኛውንም ስጋት ለመቀልበስ አስፈላጊውን አጸፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠንቅቀዋል።
 
ኔቶ ሩሲያን ለመክበብ ወደ አገሪቷ ድንበሮች የሚያደርገው መስፋፋትም ለአውሮፓ ብሎም ለዓለም ሰላም ጠንቅ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
 
ሩሰያከዚህ ቀደም ዩክሬን ኔቶንለመቀላለቀል እንቅስቃሴ መጀመሯን ተከትሎ በአገራቱ መካከል የተከሰተው ጦርነት አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን አር ቲ በዘገባው አስታውሷል ፡፡
 
ፊንላንድ ከሩሲያ ጋር ሰፊ ድንበር የምትዋሰን አገር ከመሆኗ ጋር ተያይዞም ሞስኮ ድርጊቱን በቀላሉ እንደማታየው እየተነገረ ነው፡፡
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.