Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ 60 በመቶ የሚሆነውን የመድሀኒትና የህክምና ግብዓት በሃገር ውስጥ እንደምታሟላ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣይ አምስት አመታት ውስጥ ኢትዮጵያ 60 በመቶ የሚሆነውን የመድሀኒት እና የህክምና ግብዓት በሃገር ውስጥ እንደምታሟላ ተገለጸ።

መንግስት በ10 አመቱ የሃገር በቀል ኢኮኖሚን ለማሳደግ በያዘው እቅድ የሃገር ውስጥ የፋርማሲዩቲካል አምራች ኢንዱስትሪዎች በሃገር ውስጥ የመድኃኒት እና የህክምና ግብዓት እንዲያመርቱ ያሉባቸውን ችግሮች በመፍታት ዘርፉን እንደሚደግፍ ነው የተገለጸው።

የፋርማሲዩቲካል አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍን በአዲስ ምዕራፍ ለማጠናከር ከፋርማሲዩቲካል አምራቾች እና ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተካሂዷል፡፡

የአርማወርሐንሰን የምርምር ተቋም ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ÷በመድረኩ እንደገለጹት መንግስት የዘርፉን ተግዳሮቶች በመቅረፍ ከፋርማሲዩቲካል አምራች ኢንዱስትሪው ጋር እና ባለድርሻ አካላት ጋር መምከር አስፈልጓል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው÷ ዘርፉን ደግፈን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ መንግሥት ከሚጫወተው ሚና በተጨማሪ የዘርፉ አምራቾችም በቅንጅት መስራት ይገባቸዋል ብለዋል።

ለዘርፉ የተሰጠውን ትኩረት ተጠቅመን በቀጣይ አምስት አመታት 60 በመቶ የመድኃኒት እና የህክምና ግብዓትን በሃገር ውስጥ ምርት እናሟላለን ነው ያሉት።

በቆንጂት ዘውዴ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.