Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ሊያ ታደሰ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎች የተለያዩ አካላት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ የድንገተኛ ጊዜ ምላሽ እና የማገገሚያ ምክክር ከጤና፣ ሥነ-ምግብ እና የንጽህና አጠባበቅ አጋሮች ጋር ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ውይይቱ በተለይ ግጭት ውስጥ በነበሩ የአማራ፣ አፋር፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች እንዲሁም ድርቅ በተከሰተባቸው የኦሮሚያ፣ ሶማሌ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ ክልሎች የሚደረገውን ድጋፍ ማሳደግ ላይ ያተኮረ እንደነበር አስታውቀዋል።

በዚህም በተለያዩ ምክንያቶች በተጎዱ አካባቢዎች የሚኖሩ ወገኖችን ለማገዝ የሚደረጉ የቁሳቁስና ሌሎች ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ለሁሉም ለጋሽ አጋር አካላት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.