Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በ60 ሚሊየን ዩሮ የተገነባውን የብቅል ፋብሪካ መረቁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የተገነባው ሱፍሌ ማልት የብቅል ማምረቻ ፋብሪካ ተመረቀ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ “ዛሬ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ያስመረቅነውና የኢንቪቮ ግሩፕ ኢንቨስትመንት የሚመሰገን ነው” ብለዋል።

ፋብሪካው ከ50 ሺህ ከሚበልጡ አርሶ አደሮች ጋር ትስስር በመፍጠር በዓመት 60 ሺህ ቶን ብቅል ለማምረት የሚያስችል መሆኑም በዋናነት የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርቶች ለመተካት የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ እንደሚያስችል ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ እንዲህ ባለ መጠነ ሰፊ መንገድ መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ የሚፈልጉ ቁርጠኛ ባለሀብቶችን ለመቀበል እና አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ዝግጁ ናት ሲሉም በፅሁፋቸው አስፍረዋል።

ፋብሪካው በ60 ሚሊየን ዩሮ ወጪ መገንባቱም ታውቋል፡፡

በግብርና ላይ የሚሰራ ኢንቪቮ ግሩፕ በተባለ የፈረንሳይ ኩባንያ ስር የሚገኘው ሱፍሌት ማልት በ38 ሀገራት የተለያዩ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች አሉት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.